ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በቀጣዮቹ ዐሥር ዓመታት ውስጥ 50 አዳዲስ ሃይማኖታዊ የቴሌቪዥን ስርጭቶች ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ከወዲሁ ተነገረ።
ቀደም ሲል በአዋጅ ፈቃድ እንዳያገኙ የተከለከሉ የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም ፈቃድ ሊሰጣቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ገለጸ።
ባለሥልጣኑ ከሚዲያ ተቋማት አመራሮች ጋር እያካሄደ በሚገኘው ምክክር ላይ 50 አዳዲስ ሃይማኖታዊ የቴሌቪዥን ስርጭቶች ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ይፋ ተደረገ።
በመሆኑም በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ከ100 በላይ አዳዲስ የሬዲዮ ጣቢያዎችና ለ130 የቴሌቪዥን ሥርጭቶች ፈቃድ ለመስጠት እቅድ መያዙ ተነግሯል።
ከዚህ ባሻገር በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ለሥርጭት የሚጠቀሙባቸውን የሃገር ውስጥ ቋንቋዎችን ቁጥር ወደ 82 የማሳደግ ማቀዱንም ለማወቅ ተችሏል።