የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ዘርፍ ተቋማትን መልሶ ለመክፈት ውይይት እየተደረገ ነው

የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ዘርፍ ተቋማትን መልሶ ለመክፈት ውይይት እየተደረገ ነው

 ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮቪድ 19ን ጫና ተቋቁሞ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት፣ እንዲሁም ስልጠና ዘርፍ ተቋማትን መልሶ ለመክፈት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ የቴክኒክና ሙያ ትምህትና ስልጠና ዘርፍ ተቋማት ቢዘጉም፤ በኢዱኬሽን ኢ ለርኒንግ አማካይነት ሥልጠና ሲሰጥ መቆየቱን የተቋሙ ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ገነነ አበበ ተናግረዋል።
ተቋማቱ በተዘጉበት ወቅት ከ593 ሺኅ በላይ ተከታታይ ሠልጣኞች እንዲሁም ከ800 ሺኅ በላይ የአጭር ሥልጠና ተከታታዮች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነው የነበረ ቢሆንም በኢዱኬሽን ኢ ለርኒንግ አማካይት ወደ 50 ሠልጣኞች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረግ ተችሏል ተብሏል።
በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሥልጠናቸውን አጠናቅቀው ወደ ሥራ ይገቡ የነበሩ ከ100 ሺኅ በላይ ተመራቂ ተማሪዎች በዚሁ ወረርሽኝ ሳቢያ ሳይመረቁ ቀርተዋል።
የቴክኒክና ሙያ ትምህርና ሥልጠና ዘርፍ ተቋማት በተግባር ሥልጠና ላይ ያመዘነ ትምህርት የሚሰጡባቸው በመሆናቸው ንኪኪ እንደሚበዛባቸው የሚናገሩት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ፤ ከዚህ የተነሳ የጽንሰ ሀሳብና የተግባር ስልጠና የሚሰጥባቸውን ክፍሎች የማጽዳቱ ሥራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
በዚህ መሠረት አስፈላጊው የጥንቃቄ ሥራ ከተከናወነ በኋላ በሥስት ዙሮች ስዘሥልጠና የመስጠት ሥራ እንደሚካሄድ እየተደረገ ባለው ውይይት ላይ በሃሳብ መልክ ተነስቷል።

LEAVE A REPLY