የዓለም ባንክ የሠማኒያ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ አደረገ

የዓለም ባንክ የሠማኒያ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በግብርና ሚኒስቴር ሲተገበር የቆየው የሁለተኛ ዙር የግብርና ዕድገት ፕሮግራም ፕሮጀክቶች ማስጨረሻ የሚሆን የ80 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር  ድጋፍ ስምምነት በዓለም ባንክና በገንዘብ ሚኒስቴር መፈረሙ ታወቀ።

ድጋፉ በሁለተኛ የግብርና ዕድገት ፕሮግራም በተለያዩ ክልሎች የግብርና ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ፣ አርሶ አደሩ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ የሚያስችሉና የግብርና ምርት እሴት ሰንሰለት እንዲጎለብት እየተተገበሩ ለነበሩ ፕሮጀክቶች ማስጨረሻ የሚውል ነው ተብሏል።
የድጋፉ ስምምነቱ የተፈረመው በገንዘብ  ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና ሚስተር ኦስማን ዲዮን በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር መሆኑንም የደረሰን መረጃ ያሳያል።
የዓለም ባንክ ግብርና ሚኒስቴር የአነስተኛ አርሶና አርብቶ አደሮች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ፣ የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያስችሉና በአጠቃላይ ድህነትን ለመቀነስ የሚያካሂደውን የተለያዩ ዓይነት የልማት ፕሮግራሞች በገንዘብና በቴክኒክ እየደገፈ ይገኛል።

LEAVE A REPLY