ጃዋር መሐመድ ፣ በቀለ ገርባና ሐምዛ ቦረናን ጨምሮ 18 ተከሳሾች ቃሊቲ እንዲወርዱ...

ጃዋር መሐመድ ፣ በቀለ ገርባና ሐምዛ ቦረናን ጨምሮ 18 ተከሳሾች ቃሊቲ እንዲወርዱ ታዘዘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ቅዳሜ እለት የሽብርተኝነት ክስ እንደሚመሠረትባቸው በዐቃቤ ሕግ በኩል ይፋ የተደረገባቸው ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባና ሐምዛ ቦረና ወደ ቃሊቲ እንዲወርዱ ታዘዘ።

ጉዳዮን የያዘው ፍርድ ቤቱ እነ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ 18 ተከሳሾችን ነው ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ትእዛዝ የሰጠው።
በጥበቃ በኩል ስጋት ካለ እንደሚከታተል የገለጸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የሕገ መንግሥት እና የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት፤  በችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾች እንዲቀርቡ ትዛዝ መስጠቱን ለማወቅ ተችሏል።
በችሎት ያልቀረቡት  ተከሳሾች ባሉበት ክስ ለማንበብ ለመስከረም 21 ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ጉዳዮን የተከታተለው የኢትዮጵያ ነገ የአዲስ አበባ ዘጋቢ አስታውቋል።
በዚህ መሠረት ጀዋርና በቀለ ገርባን ጨምሮ በክስ መዝገብ ውስጥ የተካተቱ ዐሥራ ስምንት ተከሳሾች ዛሬ ከሰዐት በኋላ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንደሚወርዱ ይጠበቃል።

LEAVE A REPLY