መከላከያ ሠራዊቱ ከመስከረም 30 በኋላ መንግሥት የለም በሚሉ አካላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ...

መከላከያ ሠራዊቱ ከመስከረም 30 በኋላ መንግሥት የለም በሚሉ አካላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦነግ ሊቀመንበር የነበሩት ዳውድ ኢብሳን ጨምሮ የተለያዮ የጥፋት ኃይሎች እያስተላለፉት ላለው ሰሞነኛ የጥፋት መልእክቶች ምላሽ የሆነ ማስጠንቀቂያ ከመከላከያ ሠራዊት ተሰጠ።

ሕግመንግሥቱን በጣሰ ሁኔታ በኃይል ፍላጎቱን በሚያራምድ ማንኛውም አካል ላይ መከላከያ ሠራዊቱ እርምጃ ይወስዳል ያሉት የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ፤ ይህን ለማድረግ ሠራዊቱ ዝግጁ ነው ብለዋል።
 የፖለቲካ ፓርቲዎች በፖለቲካ ቅስቀሳቸው መከላከያ ሠራዊቱን የሚመለከት አጀንዳ እንዳያራምዱ ያስጠነቀቁት ምክትል ኤታማዦር ሹሙ ፤ በሽግግር ወይም ባላደራ መንግሥት በመመስረት ሥልጣን መያዝ አይቻልም ብለዋል።
 ከመስከረም 30 በኋላ እንደፈለግኹ እሆናለሁ በሚል አካል ላይ ሠራዊቱ እርምጃ እንደሚወስድም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ከወዲሁ አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY