አቶ ልደቱ አያሌው ለማክሰኞ ቀጠሮ ተሰጠ

አቶ ልደቱ አያሌው ለማክሰኞ ቀጠሮ ተሰጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ለልደቱ አያሌው ከትናንት በስቲያ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፈቀደው የ100 ሺኅ ብር የዋስትና ፈቃድ ይግባኝ ለማቅረብ ሲባል ታገደ።

ዋስትናውን ያገደው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ሸዋ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
የአነጋጋሪው ፖለቲከኛ በዋስ የመውጣት መብት የታገደው በአዳማ ፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ህግ ዋስትናው ላይ ይግባኝ ተብሎ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ያስቀርባል በማለት ዋስትናውን በማገድ መስከረም 19 በቀጠሯቸው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አቶ ልደቱ አያሌው ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ በመያዝ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY