ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ የባህር ኃይሌን በዚህ ዓመት እውን አደርጋለሁ አለች

ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ የባህር ኃይሌን በዚህ ዓመት እውን አደርጋለሁ አለች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በያዝነው 2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ ልታቋቁም ያሰበችውን የባህር ሀይሉን እውን ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ።

ኢትዮጵያ ለዘመናት ስትጠቀምበት የኖረውን የአሰብና ምጽዋ ወደቦችን ሀገር የመበታተን ራዕይ ይዞ ትግል የጀመረው ወያኔ ሥልጣን በያዘ ማግስት ይህንን ሕልሙን እውን ለማድረግ ለሻዕቢያ ታማኝነቱን በማሳየት ሀገሪቱን ወደብ አልባ አድርጓት ቆይቷል።
በህወሓት መራሹ ኢህአዴግ የሥልጣን ዘመን ወደብ አልባ ሆና የሰነበተችው ኢትዮጵያ በዚህ ምክንያት ከጅምሩ እንዲበተን የተደረገው የባህር ኃይል እንዲበተን ተደርጎል። ይሁን እንጂ በለውጡ ማግስት ከኤርትራ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ኢትዮጵያ ምጽዋና አሰብ ወደቦችን የመጠቀም እድል በማግኘቷ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትእዛዝ የባህር ኃይሉ በአዲስ መልክ እየተቋቋመ ይገኛል።
 የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ዋና አዛዥ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ፤ በያዝነው ዓመት የባህር ኃይሉን እውን ለማድረግ ሠፊ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል። በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝ ድርሻ ያላቸው ባለ ድርሻ አካላት ለባህር ኃይሉ እንደገና መመስረት ያላሰለሰ ትብብርና ድጋፍ እንደሚያደርጉም ሓላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY