ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በቅርቡ በታጠቁ ኃይሎች በርካታ ንጹሃን ዜጎች በተገደሉባት ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን በኃላፊነት ላይ የነበሩ ሰዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።
በመተከል ዞን ከተከሰተው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ 45 አመራሮች ላይ ነው እርምጃ የተወሰደው።
በተደጋጋሚ በዞኑ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው ያለበትና በቸልተኝነት የተመለከቱ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ላይ ክልሉ ህጋዊና ፖለቲካዊ እርምጃ መወሰዱ ታውቋል።
በበመተከል ዞን ካሉ ከ45 አመራሮች መካከል 44ቱ ከኃላፊነት የተነሱ ሲሆን፤ ከነዚህ መካከልም ዐሥሩ በህግ እንዲጠየቁና ምርመራ እንዲጣራባቸው መደረጉ ተሰምቷል።
ከኃላፊነት ሳይነሳ በቀረው አንድ ሰው ላይ ደግሞ የአመራር ሽግሽግ እንደተደረገ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ ይፋ አድርጓል።