ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከሀገር ሊወጣ የነበረ 132,860 የአሜሪካን ዶላር በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋሉ ታወቀ።
የዚምባብዌ ዜጋ የሆነ መንገደኛ ገንዘብ ይዞ ስለመግባቱ ድክለር ሳያደርግ 132,860 የአሜሪካን ዶላር ይዞ ከሀገር ለመውጣት ሲሞክር በሴኩሪቲ እና በጉምሩክ ኦፊሰሮች አማክኝነት በተደረገ ጥብቅ ክትትልና ፍተሸ ሊያዝ ችሏል።
ዶላሩ ተይዞ ገቢ የተደረገ ሲሆን፣ ግለሰቡ ገንዘቡን በተለያየ መንገድና አልሙኒየም (ፎይል) በመጠቅለል ለማሳለፍ ሲሞክር ነው ገንዘቡ በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡