የአዲስ አበባ ዋና ዋና ሥፍራዎች መብራት እንደማያገኙ ተነገረ

የአዲስ አበባ ዋና ዋና ሥፍራዎች መብራት እንደማያገኙ ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሸን ነገ የአዲስ አበባ የተለያዮ ሥፍራዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኙ ገለጸ።

ሰኞ መስከረም 18/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከቀኑ 5፡00 ድረስ፡- ገርጂ ዮኒቲ ኮሌጅ፣ ቦሌ ሆምስ፣ ቦሌ ሲቪል አቬይሺን፣ ጎሮ አለማው ህንፃ ጃክሮስ፣ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አካባቢው፤  ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ8፡00 ሰዐት ድረስ ሰሚት ኮንደሚኒየም፣ ፍየል ቤት ጊዮርጊስ ቤ/ክ እና አካባቢው፣ ጎፋ ኪዳነ ነምህረት፣ መካኒሳ ቆሬ ኮንደሚኒየም፣ ቆሬ ካምፕ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ መድኃኒት ፋብሪካ፣ አየር ጤና ኪዳነምህረት፣ ዓለም ባንክ፣ ጀርመን አደባባይ፣ ሃና ማርያም፣ ሃይሌ ጋርመንት፣ቆጣሪ ኮንደሚኒየም፣ኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ ማንጎ ሰፈር፣ ላፍቶ ኢንዱስትሪ መንደር እና አካባቢው የመብራት እንደማያገኙ ከወዲሁ ታውቋል።
በተያያዘ ማክሰኞ መስከረም 19/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ5፡00 ድረስ፤ መሳለሚያ፣ እሳት አደጋ፣ሳንባ ነቀርሳ፣ አበበ ቢቂላ እስታዲየም፣ ታይዋን፣ ሆላንድ ኤንባሲ እና አካባቢው፤ እንዲሁም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ10፡00 ሰዐት ድረስ ደግሞ ሃና ማርያም፣ ሃይሌ ጋርመንት፣ ቆጣሪ ኮንደሚኒየም፣ ኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ ማንጎ ሰፈር፣ ሳሪስ አቦ ቤ/ክ፣ ቦሌ ቡልቡላ ኮንደሚኒየም፣ ቡልቡላ ማርያም ማዞርያ፣ ክሬሸር እና አካባቢው ላይ የመብራት መቋረጥ ስለሚኖር ደንበኞች ቅድመ ዝግጅት ከወዲሁ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል።

LEAVE A REPLY