የዓለም ጤና ድርጅት የከሮና ክትባት እስኪገኝ ድረስ 2 ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ...

የዓለም ጤና ድርጅት የከሮና ክትባት እስኪገኝ ድረስ 2 ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ሲል ገመተ

Ethiopian Minister of Foreign Affairs Tedros Adhanom Ghebreyesus attends a press conference launching his candidacy to the post of Director General of World Health Organization (WHO), on the sidelines of the WHO's annual assembly, on May 24, 2016, in Geneva. Delegates from 194 member-states gather for the second day of the WHO's annual assembly, with the UN agency's chief Margaret Chan warning in an opening address that the world was not prepared to cope with a rising threat from infectious diseases. / AFP / FABRICE COFFRINI (Photo credit should read FABRICE COFFRINI/AFP/Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የዓለም የጤና ድርጅት ሁነኛ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት እስኪገኝ ድረስ በዓለም ዙሪያ 2 ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ሲል ግምቱን አስቀመጠ።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ብዛት ወደ 1 ሚሊዮን እንደተጠጋም ሬውተርስ ይፋ አድርጓል።
የድርጅቱ የአጣዳፊ ጉዳዮች ሓላፊ የሆኑት ማይክ ሪያን የተረጋገጠ ክትባት እስኪገኝ ድረስ አነሰ ቢባል 2 ሚሊዮን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊሞቱ እንደሚችሉ ይናገራሉ።
በዚህ ወቅት በርካታ ክትባቶች በተለያየ የሙከራ ደረጃ ላይ ሲሆኑ፤ ድርጅቱ ሁነኛ ክትባት ሲገኝ ለድሃ ሃገሮች እንዲዳረስ ኮቫክስ የተሰኘ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር መዘርጋቱን ለማወቅ ተችሏል።
ቻይናም ይህንን ድጋፍ ማሰባሰቢያ በዋናነት እንድትደግፍ ምክክር እየተደረገ ነው ያሉት ማዬክ ሪያን፤ እስከዚያው መሰረታዊ የመከላከያ መላዎች ቸል መባል እንደሌለባቸው ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY