መቀመጫቸውን ቤኒሻንጉል ያደረጉ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎች 200 ሰዎች መጎዳታቸውን አስታወቁ

መቀመጫቸውን ቤኒሻንጉል ያደረጉ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎች 200 ሰዎች መጎዳታቸውን አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መቀመጫቸውን በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመተከል ዞን ከፍተኛ ግድያ መፈጸሙን በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ አስታወቁ።

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ በመተከል ዞን ከሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ መስከረም 8/2013 ድረስ ከ150 በላይ ዜጎች ሕይወታቸወን እንዳጡ ጥናት አድርገው ማረጋገጣቸውን በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት ሦስት የፖለቲካ ድርጅቶች ይፋ አድርገዋል።
 በክልሉ የሚንቀሳቀሱት የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ)፣ የጉምዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ሕዝብ ነፃነትና ንቅናቄ ለሰላምና ዴሞክራዊ ድርጅት (ቤሕነን-ሰዴድ) እንደተናገሩት ፤ ከሰኔ 22/2012 ጀምሮ እስከ መስከረም 8/2013 ብቻ በጉባ፣ በወንበራና በቡለን ወረዳዎች በታጣቂዎችና በፀጥታ አካላት በተወሰዱ እርምጃዎች ከ150 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና ከ50 በላይ ዜጎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

LEAVE A REPLY