ኑዛዜ || ፕሮፍ. መስፍን ወልደ ማርያም

ኑዛዜ || ፕሮፍ. መስፍን ወልደ ማርያም

የሕይወት ጽዋዬ ጥንፍፍ ብሎ ሲያበቃ
ሲቀር ባዶውን፣ የቆየ ባዶ ዕቃ
ሲበቃኝ፤ በቃህ ስባል
ትንፋሼ ሲቆም በትግል
ስሸነፍ ተሟጦ ኃይል
ሰው መሆኔ ቀርቶ፣– አስከሬን ስባል
እወቁልኝ ይህን ብቻ፣– የገባኝን ያህል
ሞክሬ ነበር ሰው ለመሆን
ሰውነት በከፋበት ዘመን
መሬት አልነበረኝም በሕይወቴ
መሬት አልፈልግም፤ አሁን በሞቴ
አቃጥሉልኝ ሬሣዬን
አመድ እስኪሆን
አዋሽ ውስጥ ጨምሩልኝ አመዴን
ከአዋሽ ይቀላቀል ከዘመዴ
ይቺን አትንፈጉኝ አደ
አመዴ እንኳን እንዲኮራ!

|| ፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም ስለ አዋሽ ታማኝነት የገለጹበት ||

LEAVE A REPLY