ከአማራ ክልል በሚመጡ አውቶቢሶች ውስጥ የተሳፈሩ ቄሮዎች እየተመረጡ እንዲወርዱ ተደረገ

ከአማራ ክልል በሚመጡ አውቶቢሶች ውስጥ የተሳፈሩ ቄሮዎች እየተመረጡ እንዲወርዱ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ቅዳሜ ይከበራል የሚባለው የእሬቻ ዋዜማን በአዲስ አበባ ለማክበር ነው የምትጓዙት በሚል ከተለያዮ የአማራ ክልል በሚመጡ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች ውስጥ የተሳፈሩ ቄሮዎች እየተመረጡ ከመኪናዎች እንዲወርዱ ተደረገ።

በጣም ጠንካራና ረዥም ሰዐታት የሚፈጀውን ፍተሻ አልፈው ወደ አዲስ አበባ መግባት በቻሉ ጥቂት የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎችን አነጋግሮ መረጃ መሰብሰብ የቻለው የኢትዮጵያ ነገ የአዲስ አበባ ዘጋቢ፤ በተለይም ከደብረብርሃን፣ አጣዬና ደብረማርቆስ ከተሞች የተነሱ አውቶቢሶች ውስጥ የነበሩ ቄሮዎች በፍተሻው ሰዐት ከመኪናው እንዲወርዱና  ወደመጡበት እንዲመለሱ መደረጉን መመልከታቸውን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ መግቢያ ላይ የነበሩ የኦሮሚያ ልዮ ኃይል፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት አውቶቢሶቹን እያስቆሙ ከፍተኛ ፍተሻ እያደረጉ መሆናቸውን (ምንም እንኳ በርካታ ሴቶች ሳይፈተሹ ቢያልፉም) የጠቆሙት መንገደኞች፤ የፀጥታ አባላቱ መታወቂያ አውጥተው ስምና ፎቶ በማስተያየት ዕድሜያቸው ወጣት የሆኑ የኦሮሚያ ተወላጆች ወጣቶችን ከጉዞ ሲገድቡ አይተናል ብለዋል።
ከአማራ ክልል በሚመጡ መንገደኞች ላይ እንዲህ አይነት እርምጃ የተወሰደው ጽንፈኛው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኦኤምኤን፤ ለእሬቻ በዓል በመላ ሀገሪቱ በየትኛውም ክልል የሚገኙ የኦሮሚያ ተወላጆች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደጋጋሚ ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ እንደሆነ ተገምቷል።

LEAVE A REPLY