ዛሬ ተፈናቃይ አርሶ አደር ናቸው ለተባሉ የኦሮሚያ ተወላጆች 20 ሺኅ ኮንዶሚኒየም ቤት...

ዛሬ ተፈናቃይ አርሶ አደር ናቸው ለተባሉ የኦሮሚያ ተወላጆች 20 ሺኅ ኮንዶሚኒየም ቤት ተሰጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የ13ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ የወጣላቸው አዲስ አበቤዎች ዛሬ ቁልፍ እንደሚረከቡ ተነገረ።

ዛሬ ከሰዐት በኋላ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የሚመለከታቸው የሥራ ሓላፊዎች በተገኙበት ለቤት ባለቤቶቹ የቁልፍ ማስረከብ  ሥነ-ሥርዓቱ ተከናውኗል።
በ13ኛው ዙር ዕጣ የወጣላቸው አዲስ አበቤዎች ለመረከብ ውል መዋዋል ቢጀምሩም ቁልፍ ሳይረከቡ እስካሁን ድረስ መቆየታቸው ይታወሳል።
በዛሬው መርሃ ግብርም በ13ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ከወጣላቸው በተጨማሪ፣ በከተማ አስተዳደሩ የጋራ መኖሪያ ቤት እንዲሰጣቸው ለተወሰነላቸው የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ቁልፍ እንዲያገኙ ተደርጓል።
ባለፈው ዓመት በታከለ ኡማ የነበረው የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በልማት ምክንያት የተነሱ አርሶ አደሮችን በቋሚነት ለማቋቋም በሚል ከ20 ሺኅ በላይ ለሚሆኑት የጋራ   መኖሪያ ቤት እንዲሰጥ ቢወስንም፤ በቅርብ በኢዜማ በኩል እንደተጋለጠው መኖሪያ ቤቶቹ ከተለያዮ አካባቢዎች ለመጡ ለኦሮሚያ ተወላጆች እንዲሰጥ መደረጉን ተከትሎ እስካሁን ድረስ እያነጋገረ ይገኛል።
ተፈናቃይ ናቸው ከተባሉት አርሶ አደሮች መካከል ከ400 በላይ የሚሆኑት ጉዳያቸው ገና  በመጣራት ላይ ነው  የተባለ ሲሆን ለ20 ሺኅ አርሶ አደሮች ዛሬ ቁልፍ ይሰጣቸዋል ቢባልም፤ አሁንም ቤቶቹ በትክክል ከተረኛነት ስሜት በፀዳ መልኩ ለትክክለኞቹ አርሶ አደር ተፈናቃዮች ይሰጣል ወይ የሚለው አሁንም በብዙዎች ዘንድ እምነት አላገኘም።

LEAVE A REPLY