ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የመረጃ ነፃነት ቀን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ለ3ኛ ጊዜ በዓለም ለ5ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ ላይም ኢትዮጵያ የመረጃ ነፃነት አዋጅን ከፈረሙ ሃገራት መካከል በአፍሪካ ቀዳሚ ብትሆንም፤ ነገር ግን ነፃነቱን ከማክበር አንፃር አሁንም ውስንነት እንዳለ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ገልጸዋል።
በክብረ በዓሉ የመገናኛ ብዙኃን መረጃን ለማግኘት እየገጠሟቸው ያሉ ተግዳሮቶችን መቅረፍ እንዳለባቸው የሚጠቁሙ የተለያዮ ሀሳቦች ተነስተዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ በኢትዮጵያ የመረጃ ነፃነት አዋጅን ከመፈረም ባለፈ አተገባበሩ ላይ ብዙ ውስንነት እንዳለበት ጠቁመው፣ በተለይም መረጃ ያለመስጠት፣ መረጃዎች በአግባቡ አለመተንተናቸው፣ ለሚዲያዎች የሚሰጡ ምላሾች ቀናት መርዘም፣ ምስጢራዊ የሚባሉ መረጃዎች ምንድናቸው የሚሉትን ለይቶ አለማስቀመጥ፣ ሚዲያዎች መረጃ እንዳያገኙ መደረጉ የችግሩ አካል ናቸው ብለዋል።