ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መስከረም 23 እና 24 የሚከበረውን የኢሬቻ በአል ለመረበሽ የተዘጋጁ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ኮማንደር አራርሳ መርዳሳ ፤ የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት በተለያየ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኃይሎች እንዳሉና ኮሚሽኑም እንደደረሰባቸው በጠቆሙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እስካሁን ድረስ 503 ሰዎች፣14 ክላሽ ፣ 26 ቦምብ እና 103 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አረጋግጠዋል።
ኅብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን ከህወሓት እና ከሸኔ የተሰጣቸውን ግዳጅ በመውሰድና ኦሮሚያን የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሀይሎችን በማጋለጥ ረገድ፤ እንዲሁም በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አሁንም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
“ከመስከረም 25 በኋላ መንግስት የለም” እያሉ ህብረተሰቡን ለማወክ የሚፈልጉ አካላት በምንም ሁኔታ አይሳካላቸውም ያሉት ጀነራል ኮማንደር አራርሳ የኦሮሚያ ፖሊስ የህዝቡን ሰላም የሚያውኩትን በመከታተል ህግ ለማስከበር በቁርጠኝነት ተዘጋጅቷል ብለዋል።