ዳሽን ባንክ 25 ሺኅ በላይ አዳዲስ አካውንቶች መከፈታቸውን ይፋ አደረገ

ዳሽን ባንክ 25 ሺኅ በላይ አዳዲስ አካውንቶች መከፈታቸውን ይፋ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዳሸን ባንክ በሁሉም ቅርንጫፎቹ መቶ በመቶ አዲሱን የብር ኖት ማሰራጨቱን እና ከ25 ሺኅ በላይ አዳዲስ የባንክ አካውንቶች መከፈታቸውን ይፋ አደረገ።

ዳሸን ባንክ አክሲዮን ባንኩ እያከናወናቸው ስላላው ጉዳዮች ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ከሁለት ሳምንታት በፊት በሁሉም ባንኮች እንዲሰራጭ የተደረገውን አዲሱን የኢትዮጵያ የብር ኖት ዳሽን ባንክ በሁሉም ቅርንጫፍ ባንኮቹ እና ከ380 በላይ የኤቴኤም ማሽኖቹ እያሰራጨ መሆኑንም ገልጿል።
ባንኩበተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹም በራሱ ተሸከርካሪዎች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን የትራንስፖርት አገልግሎት በመጠቀም እንዲሠራጭ ማድረጉን አስታውቋል።
ባንኩ እሁድን ጨምሮ በሁሉም የሥራ ቀናት እስከ ምሽት አንድ ሰዐት ድረስ አገልግሎት እየሰጠ እንሚገኝ ያስታወቀ ሲሆን፤ ባለፉት ሁለት ሳምንታት አዲሱን የብር ኖት ለመቀየር በርካታ ደንበኞች ወደ ባንኩ እየመጡ መሆናቸውም ተሰምቷል።
ይህ ደግሞ ከዚህ በፊት ከባንክ ውጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ገንዘቦችን ወደ ባንክ ሥርዓቱ እየገቡ ስለመሆናቸው ማሳያ መሆኑን የገለፁት የዳሽን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ፤ አሮጌውን የብር ኖት አመሳስሎ በመሥራት ወደ ባንክ ሊያስገቡ የነበሩ ግለሰቦችን በመቆጣጠር ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ተደርጓል ብለዋል።
ዳሸን ባንክ ማኅበራዊ ግዴታን ከመወጣት አንፃር የተለያዩ ተፈጥሮአዊ እና ሠው ሠራሽ አደጋዎች ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ የሚሆን ከ170 ሚሊዮን ብር በላይ መለገሱን፣ እንዲሁም ከመንግሥት በቀረበው ሸገርን የማስዋብ ፕሮጅት ላይ፤ የገበታ ለሃገር ግንባታ አካል የሆኑት የጎርጎራ፣ ወንጪ እና የኮይሻ ፕሮጀክቶች ላይ የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY