የግል ት/ቤቶች ከእንግዲህ በኋላ ማንኛውንም ዓይነት ክፍያ በባንክ ብቻ እንዲቀበሉ ተወሰነ

የግል ት/ቤቶች ከእንግዲህ በኋላ ማንኛውንም ዓይነት ክፍያ በባንክ ብቻ እንዲቀበሉ ተወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከእንግዲህ በኋላ የግል ትምህርት ቤቶች ማንኛውንም ዓይነት ክፍያ መቀበል የሚችሉት በባንክ ብቻ መሆኑ ተነገረ።

በዚህ መሠረት ወላጆችም የልጆቻቸውን የትምህርት ቤት ክፍያ በባንክ ብቻ መፈፀም እንዳለባቸው ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።
አሁን ላይ በአዲስ አበባ በሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች አከፋፈል ሥርዓት ዙሪያ አንዳንድ ችግሮች በበበርካታ ትምህርት ቤቶች ዘንድ መስተዋሉን የተናገሩት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ፤ አምና ሢሠራበት ከነበረው ክፍያ ላይ ጭማሪ የሚያደርጉ ትምህርት ቤቶችንም ከእንግዲህ በኋላ እንደማይታገስ አስታውቀዋል።
ወላጆች የተማሪዎችን ክፍያ በባንክ በኩል እንዲፈጸም የተወሰነው ጥቂት ትምህርት ቤቶች ከክፍያ ጋር በተያያዘ ደረሰኝ እንደማይቆርጡ በመረጋገጡና ከወርሃዊ ክፍያዎች ውጭ የሆኑ ተጨማሪ ገንዘቦችን ወላጆችን አስጨንቀው በመቀበል ላይ መሆናቸው በመረጋገጡ እንደሆነም ከሚኒስቴር ዴኤታው ማብራሪያ ለማረጋገጥ ተችሏል።
ከአሁን በኋላ ወላጆች በባንክ በኩል ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ደረሰኛቸውን በመያዝ ለት/ቤቱ በማሳወቅ ፣ ትምህርት ቤቶችም በዚህ መንገድ ወርሃዊ ክፍያ መፈጸሙን ማረጋገጥ እንደሚችሉ የተናገሩት ዶክተር ገረመው ሁሉቃ፤ ከአምናው ክፍያ ውጪ ተጨማሪ የሚጠይቁ ትምህርት ቤቶችን ኅብረተሰቡ ለሕግ አካላት እንዲያሳውቅ አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY