ዛሬ የተከበረው የሆራ ፊንፊኔ በዓል በሰላም መከበሩን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ዛሬ የተከበረው የሆራ ፊንፊኔ በዓል በሰላም መከበሩን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዛሬ ማለዳ የተካሄደው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም መከበሩን ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

አባገዳዎች፣ አደ ስንቄዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ከለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መከበሩን ኮሚሽኑ አረጋግጧል።
በዓሉ በሰላም እንዲከበር የፀጥታ ግብረ ኃይሉ ዕቅድ በማውጣት እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎቹን በማወያየት ወደ ሥራ መግባቱን ያስታወሰው ኮሚሽኑ፤ ልዩ ልዩ አካላትን ያሳተፈ የፀጥታ ሥራ በመሠራቱ በዓሉን በሰላም ማክበር ተችሏል ሲልም ተደምጧል።
ለበዓሉ ስኬታማነት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት ፣ የበዓሉ ታዳሚዎች ላደረጉት ቀና ትብብር፣ ደከመን ሰለቸኝ ሳይሉ ሕዝብና መንግሥት የጣሉባቸውን ሓላፊነት በብቃት ለተውጡ ለከተማው አስተዳደር፣ ለሀገር መከላከያ፣ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ለሪፐብሊካን ዘብ፣ ለፌደራል፣ ለኦሮሚያና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮችና አባላት በፀጥታ ግብረ ኃይሉ ስም ኮሚሽኑ ምስጋናዬ ይድረስልኝ ብሏል።
መላው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ለማስቻል መረጃዎችን ለፀጥታ ኃይሉ በማቀበል፣ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት በፖሊስ የተላለፉ መረጃዎች በመቀበልና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ተባባሪ ለነበረው ፤ (ትናንት አልፎ አልፎ ቄሮዎች በየአውራ መንገዱ ሲያደርጉት የነበረውን ነገር አዘል ጭፈራ በትዕግስት ላሳለፈው) የአዲስ አበባ ሕዝብ  ፖሊስ ኮሚሽኑ ምስጋናውን በከፍተኛ ሁኔታ አቅርቧል።

LEAVE A REPLY