ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ “ኮክቴል” የተሰኘ አዲስ ክትባት ተሰጣቸው

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ “ኮክቴል” የተሰኘ አዲስ ክትባት ተሰጣቸው

- PHOTO TAKEN 29FEV04 - Donald Trump and his girlfriend Melania Knauss arrive at the Vanity Fair Oscar party at Morton's restaurant in West Hollywood, California, February 29, 2004.

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ትናንት በኮሮና መያዛቸው የተረጋገጠው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሆስፒታል መግባታቸውን የሀገሪቱ መንግሥቱ ይፋ አደረገ።

የ74 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ መጠነኛ የድካም ስሜት ያለባቸው ቢሆንም በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ያስታወቀው ዋይት ሀውስ፤ ፕሬዝዳንቱ ለበለጠ ክትትል እና ለጥንቃቄ ሲባል ሆስፒታል ገብተዋል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ የተወሰኑ የበሽታው ምልክቶችን ከማሳየታቸው በስተቀር በመልካም ጤንነት ላይ በመሆናቸው በሆስፒታል ውስጥም ሆነው ሀገራቸውን በፕሬዝዳንትነት እየመሩ እንደሚቀጥሉ እየተነገረ ነው።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለኮቪድ-19 በሙከራ ላይ የሚገኝ “ኮክቴል” የተሰኘ መድኃኒት በመርፌ መልክ መውሰዳቸውን ይፋ ያደረገው ደግሞ ቢቢሲ ነው።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኮቪድ-19 መያዛቸውን በትዊተራቸው ይፋ ካደረጉበት ሰዐት ጀምሮ በቶሎ እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን ለገለፁላቸው ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ብለዋል።
በኮሮና መያዛቸው የተረጋገጠው የፕሬዝዳንቱ ባለቤት ሜላኒያ ትራምፕም በመልካም ጤንነት መሆናቸው ተገልጿል። የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ዋና ሓላፊ የሆነው ቢል ስቴፈንም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው እና ከመጠነኛ የጉንፋን ምልክት ከማሳየታቸው ውጪ እርሳቸውም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY