ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከመቶ ሺኅ ብር እስከ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ያለው የብር ኖት ቅያሪ ገደብ ለቀናት መራዘሙ ይፋ ተደረገ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባወጣው የብር መቀየሪያ ቀነ ገደብ መሰረት እስከ ጥቅምት 6 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺኅ ብር እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚደርሱ አሮጌ የብር ኖቶች በሁሉም ባንኮች ተቀይረው መጠናቀቅ እንደሚገባቸው አስታውቆ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ቀነ ገደቡን በ4 ቀናት በመጨመር እስከ ጥቅምት 10 ድረስ ቅያሪው እንዲዘልቅ መፍቀዱን ለማወቅ ተችሏል።
ይህንን ተከትሎ በቀሪዎቹ 15 ቀናት ኅብረተሰቡ በአቅራቢያው በሚገኝ ማንኛውም ባንክ በመሄድ የብር ቅያሬውን ማከናውን እንደሚችልም ባንኩ ይፋ አድርጓል።