ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ፈፅሞ ቅቡልነት የለውም ሲሉ የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ሩፋኤል ሽፋረ ተናገሩ።
የፌደሬሽን ምክር ቤቱ ከመስከረም 25፣ 2013 ዓ. ም. ጀምሮ የሥልጣን ዘመኑ ማብቃቱን በማስረጃነት ያቀረቡት አፈ ጉባዔው ፤ “ምክር ቤቱ ሕጋዊ መሠረት የለውም፤ ተቀባይነት የለውም፤ ተግባራዊም ሊሆንም አይችልም” ሲሉም ፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ሲል ያሳለፈውን ውሳኔ አጣጥለዋል።
ከክልል መንግሥት በታች ያሉ የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ መዋቅሮችን የማደራጀት ሥልጣን የክልሉ ነው ያሉት የትግራይ ክልል አፈ ጉባዔ፤ የፌደራል መንግሥት በቀጥታ ወደ ታች ወርዶ ሊሠራ የሚችልበት ሕጋዊ ሥልጣን የለውም ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ ሥልጣኑን ከሕገ መንግሥቱ ውጪ፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም በመስጠት ያራዘመ ስለሆነ፤ ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የለውም ያሉት አፈ ጉባዔ ሩፋኤል፤
የክልል ምክር ቤቶችም ሆኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየአምስት ዓመቱ ምርጫ ማካሄድ አለባቸው የሚል ምክንያት በማቅረብም ይከራከራሉ።