ፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ምንም ዓይነቴ ግንኙነት እንዳያደርግ በምክር ቤት...

ፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ምንም ዓይነቴ ግንኙነት እንዳያደርግ በምክር ቤት ተወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሀገሪቱን እያስተዳደረ የሚገኘው የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ አሳለፈ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ ላይ የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል መንግሥት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ኮምጨጭ ያለ ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል።
ምክር ቤቱ ይህንን ውሳኔ ሊያሳልፍ የቻለው ባለፈው ነሀሴ 30 2012 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባዔ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገ፣ እንዳልተፈጸመ እና እንደማይፀና ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።
ውሳኔውን የሚከታተል የሕገ መንግሥት ጉዳዮች እና የማንነት ጉዳዮች አጣሪ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ ውሳኔው ባለመፈፀሙ፤ አሁን ላይ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ነው ይህንን ወሳኔ ሊያሳልፍ የቻለው፡፡
በዚህ መሠረት ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል መንግሥት ላይ ሦስት ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል፤ ውሳኔዎቹም ፦
1ኛ. የትግራይ ክልል ያካሄደውን ኢ-ህገ መንግሥታዊ ምርጫ ተከትሎ ከተመሠረቱት የትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የሕግ አስፈጻሚ አካል ጋር የፌዴራል መንግሥት ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደማያደርግ ወስኗል፡፡
2ኛ. የፌደራል መንግሥት የትግራይ ሕዝብን የልማት እና መሠረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎት ማዕከል በማድረግ የከተማ እና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ሕጋዊ ተቋማት ብቻ የሥራ ግንኙነት ያደርጋል፡፡
3ኛ. የውሳኔውን አፈጻጸም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ ክትትል መደረግ እንዳለበትም ውሳኔ አሳልፏል።

LEAVE A REPLY