ትምህርት ሚኒስቴር ታጥበው ለተደጋጋሚ አገልግሎት የሚውሉ ማክሶችን ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በነፃ እሰጣለሁ...

ትምህርት ሚኒስቴር ታጥበው ለተደጋጋሚ አገልግሎት የሚውሉ ማክሶችን ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በነፃ እሰጣለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  በቅርቡ ይጀምራል የተባለውን መደበኛ የትምህርት አሰጣጥ ተከትሎ የትምርት ሚንስቴር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለሁሉም ትምርት ቤቶች ሊሰጥ መሆኑን ገለጸ።

ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በነፃ እንደሚሰጥ ያረጋገጡት የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ሐረጓ ማሞ  ናቸው።
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛው አዲስ አበባ እና ሀዋሳ ከተሞችን ማዕከል በማድረግ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እንደሚከፋፈሉ ነው የተነገረው።
የዓለም የጤና ድርጅት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችም ሃገር ውስጥ ካሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግዢ የመፈፀም ሥራ እየተከናወነ እንደሆነና  በቅርቡም ወደ ትምህርት ቤቶች እንደሚደርሱ ተገልጿል።
ለተማሪዎች የሚከፋፈለው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በተደጋጋሚ ታጥቦ ዳግም አግልግሎት መስጠት የሚችል እንደሆነም ትምህርት ሚኒስቴር ካሰራጨው መረጃ መረዳት ተችሏል።

LEAVE A REPLY