ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በቦሌ ኤርፖርት 3.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወርቅ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰማ።
1.4 ኪ ግራም መጠን ያለው ወርቅ አዲስ አበባ ከሚገኘው የካሜሮን ኤምባሲ ወደ ካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተላከ መልዕክት በማስመሰል ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር ነው በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው።
በአዲስ አበባ ኤርፖርት በኩል ወደ ካሜሮን ለመጓዝ ዝግጅት ሲያደርግ የነበረ መንገደኛ የዲፕሎማቲክ መልዕክት በማስመሰል ወርቁን ለማሳለፍ ሲሞክር በማሽን ላይ በተደረገ ፍተሻ ሊያዝ መቻሉ ታውቋል።
የተያዘው ወርቅ በወቅታዊ የብሔራዊ ባንክ የመግዣ ዋጋ ሦሥት ሚሊዮን አራት መቶ ሺኅ (3,400,000) ብር ግምታዊ ዋጋ እንደወጣለትም ከመግለጫው መረዳት ችለናል።