ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ለባለሥልጣናት መኖሪያ የተገነቡት 6 ቅንጡ ቤቶች በጨረታ ሊሸጡ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ለባለሥልጣናት መኖሪያ የተገነቡት 6 ቅንጡ ቤቶች በጨረታ ሊሸጡ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አገልግሎታቸውን አጠናቅቀው በጡረታ ለሚወጡት የቀድሞ የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት የተገነቡት ቅንጡ መኖርያ ቤቶች ሊሸጡ መሆኑ ተነገረ።

እነዚህ ዘመናዊ ቤቶች የመንግሥት ባለሥልጣናት ከሥራ ከተሰናበቱ በኋላ ለሀገር ለሰጡት አገልግሎት ቀሪ የሕይወት ዘመናቸውን በተስተካከለ ሁኔታ እንዲመሩ ታሳቢ በማድረግ ነበር የተገነቡት።
ሆኖም ዘመናዊ የመኖርያ ሕንፃዎቹ ለታለመለት  ዓላማ ስላልዋሉ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር ቤቶቹ ተሽጠው ለግንባታ ያወጣሁት ወጪ ይመለስልኝ የሚል ጥያቄ ማቅረቡ ተሰምቷል።
በሀገራችን ትልቁ የሥልጣን እርከን የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትርን ጨምሮ ለከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተብለው የተገነቡት ቄንጠኛ መኖርያ ቤቶች ቁጥር ሥድሥት መሆኑ አይዘነጋም።
በተለምዶ ሲ ኤም ሲ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ከተገነቡት 6 እጅግ ዘመናዊ ቤቶች መካከል ትልቁ 2,441 ካሬ ሜትር ላይ  ያረፈ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።
እነዚህ ሥድሥት ቅንጡ የባለሥልጣናት መኖሪያ ተብለው የተገነቡት ቤቶች፤ ለአንዱ መኖርያ ቤት ብቻ በጨረታ የመሸጫ ዋጋ መነሻ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑም እየተገለጸ ነው።

LEAVE A REPLY