ፅንፈኛ ብሔርተኞች መንግሥት የለም ባሉበት ማገስት ኢሳያስ አፈወርቂና ዐቢይ አሕመድ ጅማ ላይ...

ፅንፈኛ ብሔርተኞች መንግሥት የለም ባሉበት ማገስት ኢሳያስ አፈወርቂና ዐቢይ አሕመድ ጅማ ላይ ተገናኙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጽንፈኛ ብሔርተኞች ከመስከረም 30 በኋላ መንግሥት እንደሌለና ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ተቀባይነት እንደማይኖረው ሲቀሰቅሱ ቢሰነብቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ጅማ ላይ ተገናኝተዋል።

ሁለቱ መሪዎች እነ ጃዋር መሐመድ፣ ኦነግ ሸኔ ( ህወሓትን ጨምሮ) መንግሥት ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ እንደማይኖር ሲለፈልፉ በከረሙባት ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በቀጠሮ የተገናኙበት ሚስጢር፤ መንግሥት በሙሉ አቅሙ ሁሉንም ነገር መቆጣጠር እንደሚችል እና ሀገርም የተረጋጋች መሆኗን ለማሳየት እንደሆነ ተገምቷል።
የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ  አፈወርቂ ለሦስት ቀናት ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ሲሆን፣ ዛሬ ረፋድ ላይ ጅማ ከተማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው ጉብኝት አድርገዋል።
 የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ የማነ ገብረመስቀልንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ያካተተው የኢሳያስ አፈወርቂ ቡድን፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ያደረገውን ጉብኝት የመንግሥትን በሁለት እግሩ መቆም ያረጋገጠ መሆኑን የተረዱ የህወሓትና የጽንፈኛ ኦሮሞ ብሔርተኛ አክቲቪስቶች የኢትዮጵያና ኤርትራን ግንኙነት የሚያጠለሹ የተለያዮ ሀሳቦችን በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ሲገልጹ ታይተዋል።
ፕሬዝደንት ኢሳያስ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባደረጉላቸው ግብዣ መሆኑንም የኤርትራ መንግሥት መግለጹ ደግሞ እነዚህን ኹከት ናፋቂ ቡድኖች በእጅጉ እንዳበሳጫቸው መረዳት ተችሏል።

LEAVE A REPLY