ለ20 ዓመታት በእስር ላይ የሚገኘው ኤርትራዊው ጋዜጠኛ አማኑኤል አሥራት የፔን ኢንተርናሽናል አሸናፊ...

ለ20 ዓመታት በእስር ላይ የሚገኘው ኤርትራዊው ጋዜጠኛ አማኑኤል አሥራት የፔን ኢንተርናሽናል አሸናፊ ሆነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በበሳል ጽሑፎቹና በሰላ ትችቱ የሚታወቀው እሰረኛው ኤርትራዊው ጋዜጠኛና ገጣሚ አማኑኤል አስራት ዓለም ዐቀፉን የፔን ሽልማት አሸነፈ።

የፔን ሽልማት በሚጽፉት ወይም በሚናገሩት ነገር የሚደርስባቸውን ጫናና ጣልቃ ገብነት ተቋቁመው የበለጠ ወኔ ላሳዩ ጸሐፊዎች እውቅናን የሚሰጥ ሲሆን፤ ኤርትራዊው አማኑኤል “ዓለም ዐቀፉ ደፋር ጸሐፊ” በሚል ስያሜም ሽልማቱን እንዳሸነፈ ተገልጿል።
የአማኑኤል አሸናፊነት ይፋ የተደረገው በትናንትናው ዕለት ሲሆን፣ የፔን ፒንተር ሽልማት የዘንድሮ አሸናፊ ጃማይካዊ-እንግሊዛዊ ገጣሚ ሊንተን ክዌሲ ጆንሰን መሆኑም ታውቋል።
ገጣሚና ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ለ20 ዓመታት በእስር ላይ ያለ ጋዜጠኛ መሆኑን ተከትሎ፣ ሽልማቱም እርሱ በሌለበት የተሰጠው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በሽልማት ፕሮግራሙ ላይ የተሳተፈው የአማኑኤል ወንድም  ከጋዜጠኛው ሥራዎች አንዱ የሆነውን ግጥምም ለታዳሚዎች አቅርቧል።
ሽልማት ሰጪው ፔን ኢንተርናሽናል ጋዜጠኛ አማኑኤል በኤርትራ ያለው ማኅበራዊ ችግር፣ ፍቅርና ተስፋን በጥልቀት የሚገልጹ ሥራዎች ያቀርብ እንደነበርም ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY