መከላከያ ሚኒስቴር ሁሉንም ሕብረተሰብ የሚያገለግል ገለልተኛ ተቋም ለመፍጠር እየሠራሁ ነው አለ

መከላከያ ሚኒስቴር ሁሉንም ሕብረተሰብ የሚያገለግል ገለልተኛ ተቋም ለመፍጠር እየሠራሁ ነው አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ገለልተኛ ተቋም ለመፍጠር ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች እያከናወንኩ ሲል የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ።

ሚኒስቴሩ የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀምን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በሰጠው መግለጫ ላይ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል እኩል ለማገልገል እየሠራሁ ነው ሲልም ተናግሯል።
የህግ የበላይነትን ለማስከበርም ሠራዊቱ ከክልልና ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ተባብሮ እየሠ ስለመሆኑ የሚናገረው የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት፤ ሰሞኑን በመተከል ዞን የደረሰው ጥቃት በግለሰቦችና በጥፋት ኃይሎች አማካኝነት የተቀነባበረ መሆኑንም ይፋ አድርጓል።
አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ችግር የሚፈጥሩ አካላትን በቁጥጥር ሥር የማዋል ተግባር እያከናወንኩ ነው ያለው ሚኒስቴሩ፤ ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት የለም ሲሉ የነበሩ አካላት ኢትዮጵያን በቅጥ የማያውቁና ያልተረዱ መሆናቸውን ጠቁሞ፤ እንዲህ በማለታቸውም ያገኙት የፖለቲካ ትርፍ እንደሌለም አስረድቷል።

LEAVE A REPLY