ወሎ ዮንቨርስቲ በኪራይ አውሮፕላን የኬሚካል ርጭት እያካሄደ ነው

ወሎ ዮንቨርስቲ በኪራይ አውሮፕላን የኬሚካል ርጭት እያካሄደ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአማራ ክልል የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለማጥፋት የሚደረገውን ከፍተኛ ጥረት ተከትሎ ወሎ ዩኒቨርስቲ በኪራይ አውሮፕላን የኬሚካል ርጭት እያካሄደ መሆኑ ተሰማ።

የአንበጣው መንጋ ከመጠን በላይ ጉዳት በማድረሱ አሁን በሀገሪቱ ያሉት ሄሊኮፕተሮች በቂ ባለመሆናቸው መንግሥት ተጨማሪ አምስት ሂሊኮፕተሮችን በኪራይ ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆኑን ኢትዮጵያ ነገ መዘገቡ አይዘነጋም።
በአንበጣ መንጋው ከፍተኛ የሰብል ውድመት የደረሰ መሆኑን ተከትሎ ብዙ የኅብረተሰብ ክፍሎች በዚህ ወቅት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ተከትሎ፤ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች በአፋጣኝ እንደሚለዩም የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
አሁን ላይ ይፋ የሆኑ መረጃዎች እንደሚያሳዮት የግብርና ሚኒስቴር የፀረ አንበጣ ኬሚካል የሚረጩ 2 ተጨማሪ አውሮፕላኖች ወደ ሀገር መግባታቸውን ይፋ አድርጓል።
በአማራ ክልል የደረሰውን የአንበጣ መንጋ ለማጥፋት መንግሥት ከሚያከናውነው የኬሚካል ርጭት ባሻገር ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው የግል ሄሊኮፕተራቸውን ለኬሚካል ርጭቱ የሰጡ ሲሆን፣ ወሎ ዮንቨርስቲም ተጨማሪ አንድ ሄሊኮፕተር በመከራይት ሰብሎችን ከመንጋው ጥቃት ለመከላከል የኬሚካል ርጭት እያከናወነ ይገኛል።

LEAVE A REPLY