ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫን ዛሬ ደግሞ የህዳሴ ገደብን ጎብኝተዋል።
የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በአንድ ጊዜ 2ሺኅ 160 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፣ በዓመት ደግሞ በአማካይ 6 ሺኅ ጊጋ ዋት ሰዐት ኃይል ያመነጫል።
የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም በአሁኑ ወቅት 36 በመቶ የደረሰ ሲሆ፣ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከኃይል ማመንጫነት ባሻገር ለቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆንም ተገምቷል።
ከአንድ ወር በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬው የህዳሴ ግድብ ጉብኝት ግድቡ በያዝነው አመት ከባለፈው ሶስት እጥፍ ውሃ እንደሚይዝ ተናግረዋል።
ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ ጋር ታላቁን የህዳሴ ግድብ ዛሬ እንደጎበኙ ታውቋል።