ጃዋር ተከብቤያለሁ ማለቱን ተከትሎ እስረኛ ግለሰብን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሉ ሁለት ተፈረደባቸው

ጃዋር ተከብቤያለሁ ማለቱን ተከትሎ እስረኛ ግለሰብን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደሉ ሁለት ተፈረደባቸው

A high-profile Ethiopian activist, Jawar Mohammed is photographed during an interview, in Addis Ababa on October 25, 2019. - A high-profile Ethiopian activist at the centre of violence that left 16 people dead this week has accused Prime Minister Abiy Ahmed of acting like a dictator and said he might challenge him in elections planned for next year. (Photo by Michael Tewelde / AFP) (Photo by MICHAEL TEWELDE/AFP via Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር አወዛጋቢው ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ ” ተከብቤያለሁ” ሲል ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በተፈጠረ ኹከት የሰው ህይወት ያጠፉ ተከሳሾች በእስራት  መቀጣታቸው ተሰማ።

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቦረዳ ከተማ በህግ ጥላ ሥር የነበሩ ግለሰብ ላይ አሰቃቂ ግድያ የፈጸሙ ሁለት ተከሳሾች፣ በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገልጿል።
ቅጣቱ የተላለፈው በነፍስ ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱት መገርሳ ያሲን እና አረቢ ሻዶ በተባሉ ግለሰቦች ላይ መሆኑን የፍርድ ቤቱ ዳኛ አሸናፊ ሼዱ ይፋ አድርገዋል።
ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ጃዋር መሃመድ ተከብቤያለሁ በሚል ካስተላለፈው ጥሪ ጋር ተያይዞ ሰልፍ በመውጣት በከተማው በተፈጠረው ኹከትና ግርግር ላደረሱት የነፍስ ማጥፋት ወንጀልና ንብረት ማውደም ውሳኔው መተላለፉም ተነግሯል።
ሁለቱ ተከሳሽ ግለሰቦች በህግ ጥላ ሥር የነበሩ አንድ ግለሰብን በአስገዳጅ ሁኔታ በሃይል በመውሰድ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለመግደላቸው በዐቃቤ ህግ ማስረጃዎች መረጋገጡንም የጠቆሙት ዳኛው፤ ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን የዐቃቤ ህግ ምስክር ሊከላከሉ ባለመቻላቸውና ወንጀለኛነታቸውም በመረጋገጡ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት እያንዳንዳቸው በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል ብለዋል።
ዳኛው ይህን ይበሉ እንጂ ከእስረኛው ሟች በተጨማሪ በሐረር የተለያዮ ሥፍራዎች “የጃዋር መንጋ” በአማራ ተወላጆችና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እጅግ ዘግናኝ የሚባል ጭፍጨፋ ማከናወናቸውና በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።
በተለያዮ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተለቀቁ ጥቃቱን የሚያሳዮ ተንቀሳቃሽ ምስሎችና በቂ የሰው ምስክሮች ቢኖሩም በሐረር ለተገደሉ ንጹሃን ዜጎች ትክክለኛ ፍርድ በሌሎች ላይ አለመሰጠቱ በሀገሪቱ ያለውን የሕግ አፈጻጸም ጥያቄ ያስነሳበታል ተብሏል።
በተመሳሳይ በአርሲ፣ በባሌ፣ በአምቦ፣ በሻሸመኔና በተለያዮ የኦሮሚያ ዞኖች በወቅቱ የጃዋር መሐመድ ደጋፊዎች በግፍ ጨፍጭፈው ለገደሏቸው ከ90 በላይ ለሚሆኑ ንጹሃን ዜጎች ወንጀለኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ሳይወሰድ ከቀረ ድፍን አንድ አመት ሊሞላው ሀያ ቀናት ብቻ ቀርተዋል።

LEAVE A REPLY