ዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት ለኮሮና ቫይረስ ክትባት የሚውል 12 ቢሊዮን ዶላር አፀደቀ

ዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት ለኮሮና ቫይረስ ክትባት የሚውል 12 ቢሊዮን ዶላር አፀደቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባት የሚውል 12 ቢሊየን ዶላር ማፅደቁ ተነገረ።

ባንኩ ሀገራቱን በፋይናንስ የደገፈው ክትባቱ ዝግጁ በሚሆንበት ወቅት እንዲገዙበት እና እንዲያሰራጩበት፣ እንዲሁም ለዜጎቻቸው ለኮሮና ቫይረስ ምርመራ እና ክትትል እንዲያውሉት መሆኑም ታውቋል።
አሁን ይፋ የተደረገው ድጋፍ ባንኩ እስከ 2021 ድረስ ለታዳጊ ሀገራት ለመስጠት ቃል ከገባው 160 ቢሊየን ዶላር ውስጥ የሚካተት ሲሆን፤ ድጋፉ በደሃ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች የክትባቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ተብሎ ተስፋ ተደርጎበታል።
የባንኩ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ ድጋፉ ሀገራቱ ፍትሃዊ የሆነ የክትባት ተደራሽነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመው፤ ባንኩ ኢኮኖሚያቸው የተጎዳ የግል ዘርፎችን ጨምሮ በኮሮና ቫይረስ አማካኝነት ተፅዕኖ ላረፈባቸው ታዳጊ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱንም አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY