ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በዚህ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ ሰብሎችን እያወደመ የሚገኘው የበረሃ አንበጣን ለመከላከል አራት አውፕላኖች በኪራይ ኢትዮጵያ መድረሳቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአሁኑ ሰዐት ከፍተኛ መጠን ያለው የአንበጣ መንጋ በምስራቅ ፣ሐረርጌ እና ሶማሌ ክልል አካባቢዎች መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
ኢትዮጵያ ከደረሱት አራት አውሮፕላኖች ሦስቱ ሥራ ላይ መሆናቸውን የገለፁት የግብርና ሚኒስቴር ዲኤታ ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሤ፤ በአፋር ክልል የተከሰተው የአንበጣ መንጋን በአመዛኙ መቆጣጠር እንደተቻለ አረጋግጠዋል።
በዚህ ወቅት በምስራቅ ሐረርጌ ፣ ድሬዳዋ እና ሱማሌ ክልል ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ መኖሩን የጠቆሙት ሚኒስቴር ዲኤታው፤ የኪራይ አውሮፕላኖቹ በኬሚካል ርጭቱ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንደሚኖራቸው ገልፀዋል።