ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ለሦስት ቀናት ጉብኝት ኢትዮጵያ የሚገኙት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ አስጎብኝነት የእንጦጦ ፓርክን ጎበኙ።
ፕሬዝዳንቱ ኢሳያስ በዚህ ሳምንት የተመረቀውን የእንጦጦ ፓርክን ፕሮጀክቱ ከመጀመሩ በፊት፣ እንዲሁም ፕሮጀክቱ በመሠራት ላይ እያለ እና አሁን የተጠናቀቀውን የፓርክ ጉብኝት ጨምሮ ለሦስት ጊዜ ጎብኝተውታል።
የእንጦጦ ፓርክ ለአንድ ዓመት ያህል ግንባታው ሲካሄድ ቆይቶ መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም በጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አህመድ ተመርቆ ለህዝብ ክፍት መሆኑ ይታወሳል።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በቆይታቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብን እና የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን መጎብኘታቸውም አይዘነጋም።