ትምህርት ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስኮችን አከፋፈለ

ትምህርት ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስኮችን አከፋፈለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በቅርቡ ትምህርት ለማስጀመር የተዘጋጀው ትምህርት ሚኒስቴር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን አከፋፈለ

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስቀጠል ትምህርት ሚኒስቴር በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተመረቱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በዐሥሩ ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ የመንግሥትና የግል ት/ቤቶች እያከፋፈለ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ በአዲስ አበባ ያለውን ሥርጭት አለመቀነሱን ተከትሎ፣ እንዲሁም በተለያዮ ክ/ሀገራት የቫይረሱ ሥርጭት እንደ አዲስ መጀመሩን ተከትሎ በቀጣይ በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ግርሻ ሊኖር ይችላል በሚል ወላጆች ከፍተኛ ስጋት ላይ ናቸው።
ኢትዮጵያ ነገ ያነጋገራቸው አንድ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስኮችን ማከፋፈሉን በበጎ ጎኑ ቢያነሱትም ተማሪዎቹ ወደ ትሞህርት ቤት ከገቡ በኋላ በተለይም ለሕጻናት ስለሚደረግላቸው ጥንቃቄና ክትትል ጥርጣሬ እንዳላቸው አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY