የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በከተማና በገጠር በአንድ ሳምንት ውስጥ ትምህርት አስጀምራለሁ አለ

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በከተማና በገጠር በአንድ ሳምንት ውስጥ ትምህርት አስጀምራለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን የመማር ማስተማሩን ሥራ ለማስቀጠል በመንግሥት፣ በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር የተቀመጡ የኮቪድ-19 መከላከል መሥፈርቶችን በማሟላት ሁሉም ትምህርት ቤቶች መደበኛ የመማር ማስተማር ለመጀመር ዝግጅታቸውን መጠናቀቃቸውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ገለፀ።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ሓላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሐመድ፤ በድሬዳዋ አስተዳደር የትምህርት ሥራውን ለማስጀመር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለመማር ማስተማሩ የሚያግዙ ግብዓቶችን የማሟላት፣ የተሰባበሩ ወንበሮችን የመጠገን፣ ትምህርት ቤቶችን የማደስና ተጨማሪ የማስተማሪያ ክፍሎችን የማመቻቸት ተግባር መከናወኑን አስረድተዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ ራሳቸውን በመጠበቅ የተቋረጠውን የትምህርት ሥራ በማካተት የተሻለ ውጤት አስመዝግበው፣ የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ እንዲቻል ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲልም ይፋዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
የድሬደዋ ሳቢያን ቁጥር ሁለት ት/ቤት ርዕሰ መምህር ወንድወሰን ንጉሤ፤ ትምህርት ቤቱ ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ያጠቀቀ መሆኑን ገልጸው፤ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ተደጋግፎ የኮሮና ቫይረስን ለማጥፋት በሚደረገው ትግል ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅዖ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
በቀጣይ ሳምንት በገጠር ቀበሌዎች ትምህርት ቤቶች የሚከፈት ሲሆን፣ ከጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ በከተማ ቀበሌ ውስጥ ያሉት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማሩን ሥራ እንደሚጀምሩም ታውቋል።

LEAVE A REPLY