የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞቹን የምግብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞቹን የምግብ

 ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ለኢትዮጵያ አቪየሽን ግሩፕ የምግብ አገልግሎት ለመስጠት የአገር ውስጥ የግብርና ምርቶችን መደገፍ የሚያስችል የጋራ ስምምነት በአሜሪካ መንግስት እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ መካካል መደረጉ ተነገረ።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረ ማርያም እና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ማይክል ሬይነር ስምምነቱን ፊርማ አኑረዋል።
ስምምነቱ የአገር ውስጥ ገበሬዎችን በቴክኖሎጂ የታገዘ ምርትን በማምረት ብዛት ብቻ ሳይሆን ጥራት ያለውን የግብርና ምርት ለአየር መንገዱ የምግብ ፍጆታ የሚያቀርቡበትን አቅም ለመፍጠር እንዲያስችል  የሚያደርግ መሆኑን አምባሳደር ማይክል ሬይነር አስረድተዋል።
 አየር መንገዱ ከውጪ የሚያመጣቸውን የምግብ ተረፈ ምርቶች በአገር ውስጥ በግብርና ምርቶች ለመለወጥ እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፤ ይህ ስምምነት ለተጓዦች የምግብ ፍጆታ በዓመት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚወጣውን የገንዘብ መጠን የማስቀረት አቅም እንደሚኖረውም ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመንገደኞች በቀን 15 ሺኅ ምግብ እንደሚያቀርብ ዋና ሥራ አስፈጻሚው በስምምነቱ ላይ ይፋ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY