ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያና ጅቡቲ የጋላፊ ጅቡቲ መንገድ አካል የሆነውን የዲክኒል ዳጉሩ 80 ኪሎ ሜትር መንገድን ለመሻሻል ሰምምነት መደረጉ ተሰማ።
ከኢትዮጵያ ድንበር እስከ ጅቡቲ ወደብ ከሚገኘው 220 ኪሎ ሜትር መንገድ ውስጥ ከዲክኒል እስከ ዳጉሩ የሚገኘው ይህ 80 ኪሎ ሜትር መንገድ የተጎዳና ለትራንስፖርት እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነ ነው የተገለጸው።
በመሆኑም ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ጉዞ አስቸጋሪ፣ የተራዘመ ጊዜ የሚወስድና ተሸከርካሪዎች በተደጋጋሚ እንዲጎዱ ከማድረጉ ባሻገር ለበርካታ አደጋ የሚያጋልጥ ጭምር መሆኑ ይታወቃል።
ችግሩን ለምፍታትም ሁለቱን ሃገራት በመወከል የጅቢቲ ፖርት ኮሪደር ሮድስ ዋና ዳይሬክተር አብዲ ኢብራሂም ፋራህ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው መፈራረማቸው ተሰምቷል።
በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ሚንስትር ዳግማዊት ሞገስ እና የጅቡቲ ፖርትስ ፍሪዞን ባለሥልጣን አቡበከር ኡመር ሀጂ ተገኝተው ሁለቱን ወገኖች ሲያፈራርሙ ታይተዋል።