ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመተከል ዞን ስላለው አስከፊ ችግር ዘግይተው ውይይት ጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመተከል ዞን ስላለው አስከፊ ችግር ዘግይተው ውይይት ጀመሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መፍትኄ ለጠፋለት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ችግር መላ ለመፈለግ ውይይት ማድረጋቸውን ይፋ አደረጉ።

የብልፅግና ፓርቲ መሥራችና መሪ ውይይቱን ያካሄዱት ከአማራ እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና ከፀጥታ ሓላፊዎች ጋር መሆኑን በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አስነብበዋል።
የተካሄደው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመተከል ዞን እየተከሰቱ ባሉት ግጭቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የሚታዮትን ችግሮች ፈትሸን፣ የአካባቢውን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል” ሲሉም በውይይቱ ላይ ተስፋ ሰጪ ነገር መታየቱን ገልጸዋል።
በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን ባለፉት ወራት አንድ ብሔርና ሃይማኖት ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የደረሱትን ተደጋጋሚ ጥቃቶች (በተለይም በቅርቡ በአንድ ሳምንት ውስጥ የተደረገው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ሳይረሳ) ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ድረስ አንዳችም መግለጫ ሳይሰጡ መሰንበታቸው በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል።

LEAVE A REPLY