ሁሉም ዮንቨርስቲዎች ከጥቅምት 23- 30 የተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ትዕዛዝ ተሰጠ

ሁሉም ዮንቨርስቲዎች ከጥቅምት 23- 30 የተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ እንዲያካሂዱ ትዕዛዝ ተሰጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮቪድ-19 ቫይረስ ሥርጭትን እየተከላከሉ ትምህርትና ስልጠናን ለማስቀጠል ውሳኔ ላይ በመደረሱ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች  ከጥቅምት 23 እስከ 30፣ 2013 ድረስ  የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች  ቅበላ እንዲያካሂዱ ታዘዙ።

መመሪያውን ያስተላለፈው  የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ አሁን ባለው አማራጭ መንገድ ወረርሽኝን እየተከላከሉ መደበኛ ትምህርት ግዴታ መሆኑን አስታውቋል።
ከቀናት በፊት በኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መሠረት በተካሄደው የተቋማት ድጋፍና ምልከታ ውጤት፤ በአንድ አንድ ተቋማት የታዩት ክፍተቶች በፍጥነት ተሟልተው፣ በግልጽ መርሃ ግብር ለተማሪዎች ቅበላ እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል።
በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የምክክር መድረክ ኮቪድ-19 እና የሠላም ጉዳይን አስመልክቶ ስጋቶች መኖራቸውን ተከትሎ  ሠፊ ውይይት ተደርጓል ነው የተባለው። ይህንን ችግር ለማስወገድ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች እና በየደረጃው ያሉት ባለድርሻ አካላት  ከሚኒስቴሩ እና ከተቋማቱ ጋር በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ ቀርቧል።

LEAVE A REPLY