ነገ (ሰኞ) በአዲስ አበባ ከተማ 560 የግል ማኅበራት አውቶቢሶች ወደ ስምሪት ይገባሉ

ነገ (ሰኞ) በአዲስ አበባ ከተማ 560 የግል ማኅበራት አውቶቢሶች ወደ ስምሪት ይገባሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት ችግር ለመቅርፍ ከነገ ጀምሮ 560 የግል ማህበራት አውቶብሶች በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ ተነገረ።

የከተማ አስተዳደሩ ከግል የትራንስፖርት ማኅበራት ጋር ስምምነት በማድረግ ነው አውቶብሶቹ በኪራይ ወደ ስምሪት እንዲገቡ የተደረገው።
ይህን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የስምሪት ፕሮግራሙ ይፋ ተደርጓል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በትራንስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ ድርሻ ባለው አንበሳ አውቶቢስ አማካይነት ተጨማሪ አንበሳ አውቶቢሶችን በሀገር ውስጥ ለማሠራትና ከውጭም ለማስገባት እቅድ መያዙ ታውቋል።

LEAVE A REPLY