የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለ50 ሚሊዮን ሰዎች ሰብኣዊና ቁሳዊ ድጋፍ አድርጊያለሁ አለ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለ50 ሚሊዮን ሰዎች ሰብኣዊና ቁሳዊ ድጋፍ አድርጊያለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የኮሮና ቫይረስን ጨምሮ ሌሎች በሀገሪቱ በተከሰቱ ችግሮች ለተጎዱ ወገኖች ከ50 ሚሊየን የሰብዓዊና ቁሳዊ ድጋፍ አድርጊያለሁ አለ።

የማኅበሩ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ እንግዳ ማንደፍሮ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ለተጎዱ የሕብረተሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የተለያዩ አካላት እገዛ እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በሀገሪቱ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ እገዛዎችን በተመለከተ እያደረገ ያለው አስተዋፅዖ ቀላል የሚባል አለመሆኑን የጠቆሙት አቶ እንግዳ፤ በቅርቡ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ጨምሮ ማኅበሩ ሌሎች አደጋዎችን ለመከላከል ባደረገው ጥረት ከ50 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን መርዳት ችሏል ብለዋልተ
የቀይ መስቀል ማኅበር ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ የተለያዩ ገቢዎችን እያሰባሰበ የሚያሰራጭ ቢሆንም ካለው ችግር አንፃር በቂ አለመሆኑ ነው የተነገረው። በተለይ ተቸግረው ያሉ ሕብረተሰቦችን በዘላቂነት ከችግሩ ለማውጣት ለሚደረገው ጥረት በከተማ አካባቢ ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች እና የተለያዩ ተቋማት አባል በመሆን የሰብዓዊ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በሀገሪቱ የሚከሰቱና ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን በማስጠናት የተለያዩ ቀድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያደረገ ሲሆን፣ ማኅበሩ ከ200 ሺኅ በላይ በጎ ፍቃደኞች እና ከ600 ሺኅ በላይ አባላት እንዳሉት ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY