መንግሥታቸው የዋጋ ግሽበት መጠኑን ዝቅ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ዐቢይ አሕመድ ይፋ አደረጉ

መንግሥታቸው የዋጋ ግሽበት መጠኑን ዝቅ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ዐቢይ አሕመድ ይፋ አደረጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሁን ሥልጣን ላይ ያለው ብልፅግና ፓርቲና መግሥታቸው የዋጋ ግሽበት መጠኑን ዝቅ ማድረግ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

“ሠፊ ሥራ የሚፈልገው የዋጋ ግሽበት ነው፤ ባለፉት ሦስት ወራት መቀነስ ያመላክታል። ግን ይህ በቂ አይደለም” በማለት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ለዚህ እንደማሳያ፤ ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቆጦች ላይ ባለፈው ሐምሌ የነበረው የዋጋ ግሽበት መጠን 22 በመቶ፣ ነሐሴ ወር 20 በመቶ፣ እንዲሁም መስከረም ወር 18.7 በመቶ መሆኑን ገልፀዋል።
ባለፉት ሦስት ወራት ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች የተመዘገበው የግሽበት መጠን እየቀነስ ቢሆንም ይህ ግን በቂ አይደለም ነው የተባለው።
በምግብ ምርቶች ላይም በተመሳሳይ ባለፉት ሦስት ወራት የዋጋ ግሽበት መጠኑ እየቀነሰ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ሐምሌ ወር 24.9 በመቶ፣ ነሐሴ ወር 22 በመቶ እንዲሁም መስከረም ላይ ደግሞ 21 በመቶ መሆኑን ለምክር ቤት አባላት አስረድተዋል።
የዋጋ ግሽበቱን መጠን ለመቀነስ በቅድሚያ ለዋጋ ግሽበቱ ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸው የሚለውን መለየት ያስፈልጋል የሚሉት ጠቅላዮ፤ የግብርና ምርት ውጤቶችን ማሳደግ ደግሞ  የዋጋ ግሽበቱ መጠን ለመቆጣጠር ሌላኛው መፍትኄ ነው ብለዋል።

LEAVE A REPLY