ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የ6 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
የኢንደስትሪ ዘረፉ ደግሞ ከፍተኛውን ዕድገት ካስመዘገቡ ዘርፎች መካከል ቀዳሚው መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ በ2012 የበጀት ዓመት 3 ነጥብ 37 ትሪሊየን ብር ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መመዝገብ ተችሏል ብለዋል።
በሀገሪቱ የነፍስ ወከፍ ገቢ 1 ሺኅ ዶላር መድረሱን ተከትሎ ይህም መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ኢትዮጵያን ማሰለፏን ያረጋግጣል ያሉት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤
በትግራይ እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረረ መምጣቱን አስታውሰው፤ “የትግራይ ሕዝብ በከፍተኛ ችግር እና ድህነት ውስጥ ያለ ሕዝብ ነው፤ በሠላም እና ልማታዊ ሆኖ የመኖር መብት አለው፤ መለወጥ ይፈልጋል” ሲሉም ተደምጠዋል።
ከትግራይ ክልል ጋር የተከሰተው አለመግባባት “በሕግ እና ሕግ ብቻ እንደሚመለስ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የፌዴሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚሰጡት ውሳኔ ላይ ብቻ በመመሠረት ጉዳዩ በሕግ የሚመለስ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚከሰቱት ጥቃቶች ውስብስብ መሆናቸውን በፓርላማው ለቀረበላቸው ጥያቄ ላይ በሰጡት ምላሽ ያብራሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ በክልሉ ያለው አለመረጋጋት ከሕዳሴ ግድብ ጋር እንደሚገናኝም አስታውሰው፤ ” ችግሩ ከህዳሴ ጋር ይገናኛል። የህዳሴን መንገድ መቁረጥ ጋር ይያያዛል። ችግር በሚያጋጥምባቸው ስፍራዎች የመኪና መንገድ አለመኖሩ ሌላው ችግር ነው።
በዚም ምክንያት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጥቃት የተፈጸመበት ቦታ ለመድረስ እስከ 7 ሰዐት ድረስ በረዣዥም ሳር ውስጥ በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል” ብለዋል።
“ጥቃቱ የሚፈጸመው በቀስት ነው፣ ሳቫና ግራስ ላንድ ውስጥ። ብዙ መስዋእትነት ተከፍሏል” ሲሉ የተናገሩት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች መማረካቸውን እና ብዙዎቹ ጥቃት አድራሾች ደግሞ መሸሻቸውን ይፋ አድርገዋል።