ለአንድ ወር በዘመቻ መልክ በተካሄደ የኮሮና ምርመራ ከ73 በመቶ በላይ ሰዎች ቫይረሱ...

ለአንድ ወር በዘመቻ መልክ በተካሄደ የኮሮና ምርመራ ከ73 በመቶ በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኘባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ በዘመቻ መልክ በተካሄደ ምርመራ ከ73 በመቶ በላይ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተነገረ።

በሀገራቱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ በተለያዩ ጊዜያት የአገሪቱ የምርመራ አቅም እያደገ የመጣ ቢሆንም፣
ነገር ግን በቅርቡ የምርመራ መጠኑ ቀንሶ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን ብቻ ለይቶ በመመርመር ውጤት እንደተገኘ ነው የተገለጸው።
ለአንድ ወር ያህል በዘመቻ መልክ በተካሄደው የኮቪድ 19 ምርመራ ከ73 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የተሠራ አጠቃላይ ሥራዎችን በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ነው ይህ የተሰማው።
ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ በጤና ሚኒስቴርና ሌሎች ተቋማት የተለያዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውና ውጤትን እንደተገኘበት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ ተናግረዋል፡፡
እስካሁን በተካሄዱ ምርመራዎች ኮቪድ 19 በህብረተሰቡ 95 በመቶ መሰራጨቱን የገለፁት የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ ፤ ባለፉት 2 ሳምንታት ብቻ በኢትዮጵያ የተካሄዱ የኮቪድ ምርመራ ውጤቶች የሚያሳዩትም በኮሮና የሚያዙ ሰዎች መጠን 10.4 በመቶ እንደሆነ አስረድተዋል።
በተለይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መነሳት ተከትሎ የትራንስፖርትም ይሁን ሌሎች እንቅስቃሴዎች እንደቀድሞ በመሆናቸው እንዲህ ዓይነት ውጤቶች ለመመዝገብ ምክንያት መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ናቸው።
ቫይረሱ በኢትዮጵያ ሲከሰት የመመርመሪያ አንድ ላብራቶሪ ያልነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዐት በተለያዩ ቦታዎች የተደራጁ 60 የሚሆኑ የኮቪድ መመርመሪያ ላብራቶሪዎች መኖራቸውን ከመግለጫው መረዳት ችለናል።
የኮሮና ቫይረስ በኅብረተሰቡ ያለውን ሥርጭት በተመለከተም ለ1 ወር በተካሄደው ዘመቻ ከ36 ሺኅ 000 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ከያዝነው ወር መገባደጃ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ሲከፈቱ ወላጆች የሚያደርጉትን ጥንቃቄ ይበልጥ ጠበቅ በማድረግ፣ የህመም ስሜት ያላቸው ልጆችን ወደ ተማሪ ቤት ባለመላክና የህክምና ክትትል እንዲያገኙ በማድረግ እንዲተባበሩ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ መልዕክት አስተላልፈዋል።

LEAVE A REPLY