የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለ43 ሺኅ ዜጎች የሥራ ዕድል...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለ43 ሺኅ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሪያለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 8ኛ ዓመት መደበኛ ጉባኤ ላይ፤ በንግድ ሥርዓቱ 3 ሺኅ 356 የንግድ ድርጅቶች ላይ የተለያዩ ህጋዊና አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃዎች መወሰዳቸው ተሰምቷል። ጉባኤው በአራት አጀንዳዎች ዙሪያ እንደሚመክርም ነው የተነገረው።

እየተካሄደ ባለው ጉባኤ የመጀመሪያ አጀንዳው ወ/ሮ ዘርፈሸዋል ንጉሤን አፈ ጉባኤ አድርጎ በአብላጫ ድምፅ የሰየመ ሲሆን፣ ምክር ቤቱ በሁለተኛ አጀንዳው የ2013 ዓ.ም ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን  እንዳደመጠ ታውቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በገቢው ዘርፍ ባለፉት ሦስት ወራት 9 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡ ይህ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ428 ሚሊዮን ብር እድገት እንዳለው ሪፖርቱ ያሳያል።
እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ሲያቀርቡ፤ የኮሮና ቫይረስ በግብር ከፋዩ ሕብረተሰብ ላይ ያደረሰውን ጫና ለመቀነስ የከተማው ካቢኔ በወሰነው ውሳኔ መሰረት የግብር እፎይታ እና የእዳ ስረዛ ተግባራዊ ተደርጓል ብለዋል።

LEAVE A REPLY