የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ግዳጅ በፍጥነት የሚያከናውኑለት ሁለት ተጨማሪ ዕዞች አደራጀ

የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ግዳጅ በፍጥነት የሚያከናውኑለት ሁለት ተጨማሪ ዕዞች አደራጀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሚሰጠኝን ግዳጅ በፍጥነት ማከናወን ያስችሉኛል በሚል ተጨማሪ ሁለት ዕዞች ማደራጀቱን ይፋ አደረገ።

በልዮ ሁኔታ የተዋቀሩት አዲሶቹ ዕዞች በዚህ ዓመት ወደ ሥ እንደሚገቡም ነው የተነገረው።
የሃገር መከላከያ ሠራዊት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሐመድ እና የሠራዊቱ የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ለመገናኛ ብዙሃን  ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የለውጥ ሥራዎች፣ በሠራዊቱ አደረጃጀትና በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ የሰጡት አመራሮቹ፤ ሠራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ በፍጥነት ማከናወን እንዲችል ሁለት አዳዲስ ዕዞች መደራጀታቸውን ይፋ አድርገዋል።
ዕዞቹ በውስጥም በውጭም የሚቃጡ ጥቃቶችና ችግሮችን ፈጥነው ለመከላከል እንዲችሉ ታስቦ የተደራጁ ናቸው ያሉት ጀነራል መሐመድ አደም፣ ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ አዲስ የተደራጁት ዕዞች ሲሆኑ የቀደሙት ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ምስራቅ ዕዞችም መኖራቸውን ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY