132 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ዛሬ ከቤይሩት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተነገረ

132 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ዛሬ ከቤይሩት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተነገረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || 132 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ዛሬ (ጥቅምት 11 ቀን) 2013 ዓም ማለዳ ከቤይሩት ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተረጋገጠ።

ኢትዮጵያዊያኑ ተመላሾች ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አወሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የሴቶችና ሕጻናት ጽ/ቤት ዳይሬክተር ጀነራል ወ/ሮ አልማዝ ገበያው እና የሚመለከታቸው መ/ቤት የሥራ ሓለፊዎች በቦታው  አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ዜጎች በ9ኛው ዙር የማስመለስ ፕሮግራም አማካኝነት የተከናወነው
በዘጠነኛው ዙር የማስመለስ ፕሮግራም መሆኑን የጠቆመው ዜና፤ በአጠቃለይ 3 ሺኅ 289 ኢትዮጵዊያን ዜጎቻችንን ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ሥራ መገባቱን ያሳያል።
በአሁኑ ሰዐት በተለያዮ አረብ ሀገራት ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚገኙ ሲሆን፣ በሳዑዲ አረቢያ ብቻ ከ20 ሺኅ በላይ ኢትዮጵያውያን በተለያዮ እስር ቤቶች ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ይገኛሉ።

LEAVE A REPLY